አደገኛ ድርጅቶች እና ግለሰቦች

የፖሊሲ ዝርዝሮች

መዝገብ ይቀይሩ
የፖሊሲ ምክንያት
የገሃዱ-ዓለም ጉዳትን ለመከላከል እና ለማክሸፍ በምናደርገው ጥረት፣ የሁከት ተልዕኮ የሚያውጁ ወይም ጥቃት ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በኛ መድረኮች ላይ እንዲኖሩ አንፈቅድም። እነዚህን ህጋዊ አካላት በመስመር ላይ እና ከመስመር ውጪ ባላቸው ባህሪ ላይ በመመስረት፣ በዋናነት ደግሞ ከሁከት ጋር ያላቸው ግንኙነትን በተመለከተ እንገመግማቸዋለን። በዚህ ፖሊሲ ስር፣ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና የሰዎች ጥምረቶችን እንሰይማለን። እነዚህ ስያሜዎች የይዘት ተፈጻሚነት ደረጃን በሚያመለክት አኳኋን ወደ ሁለት እርከኖች ይከፈላሉ፣ እርከን 1 ከየትኛውም በላይ ሰፊ ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለው እነዚህ ህጋዊ አካላት ከመስመር ውጪ የሚደርስ ጉዳት ጋር ከየትኛውም የላቀ ቀጥተኛ ትስስር አላቸው ብለን ስለምናምን ነው።
እርከን 1 ከባድ የመስመር ውጪ ጉዳቶች ላይ የሚሳተፉ ህጋዊ አካላት ላይ ትኩረት ያደርጋል - ይህም በንጹሃን ላይ ጥቃት እንዲደርስ ማመቻቸት ወይም ማነሳሳት፣ ጥበቃ በሚደረግላቸው ባህሪያት ላይ በመመስረት ሰዎችን በተደጋጋሚ ስብዕናቸውን ማንቋሸሽ ወይም ጉዳት እንዲደርስባቸው ማበረታታት፣ ወይም ስርዓታዊ የወንጀል ተግባራት ላይ መሳተፍን ያጠቃልላል። እርከን 1 የጥላቻ ድርጅቶችን፤ ወንጀለኛ ድርጅቶች፣ በአሜሪካ መንግስት በልዩ ሁኔታ ናርኮቲክስ አዘዋዋሪ ኪንግፒንስ (SDNTKs) ተብለው የተሰየሙትን ጨምሮ፤ እንዲሁም አሸባሪ ድርጅቶችን፣ በአሜሪካ መንግስት የውጪ አሸባሪ ድርጅቶች (FTOs) ወይም በልዩ ሁኔታ ዓለም አቀፍ አሸባሪዎች (SDGTs) ተብለው የተሰየሙ ተቋማት እና ግለሰቦችን ጨምሮ ያካትታል። ግልጽ ያልሆኑ ዋቢያቸውን ጨምሮ እርከን 1 ላይ ለተጠቀሱት አካላት፣ መሪዎቻቸውን፣ መስራቾቻቸውን ወይም ታዋቂ አባላቶቻቸውን ማወደስ፣ መደገፍ እና መወከል እናስወግዳለን።
በተጨማሪም፣ Meta ጥሰት የሚፈጽሙ የጥቃት ክስተቶች ብሎ የሰየማቸውን ክስተቶች ማለትም - የአሸባሪ ጥቃቶች፣ የጥላቻ ክስተቶች፣ የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ወይም የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ሙከራ፣ የጅምላ ግድያዎች፣ ወይም የጥላቻ ወንጀሎችን ጨምሮ እነዚህን የሚያደንቅ፣ የሚደግፍ፣ ወይም የሚወክል ይዘትን አንፈቅድም። እንዲሁም (1) እነዚህን ጥቃቶች የፈጸሙ አካል(ላት)ን አድናቆት፣ ድጋፍ እና ውክልና መስጠትን፤ (2) ከእንደዚህ አይነት ጥቃቶች ጋር በተገናኘ በወንጀለኛ የመነጨ ይዘትን፤ ወይም (3) በሚታዩ ተጎጂዎች ላይ እንደዚህ ዓይነት ጥቃቶች የተፈጸሙበትን ጊዜ የሚያሳይ የሶስተኛ ወገን ምስሎችን አንፈቅድም። እንደ ናዚስምን እና የነጭ የበላይነትን የመሳሰሉ ጥላቻን የሚሰብኩ ርዕዮተ አለሞችን የሚያወድስ፣ የሚደግፍ ወይም የሚክል ይዘትንም እናስወግዳለን። ወደ እነዚህ የተፈረጁ ክንውኖች ወይም ርዕዮተ አለሞች የሚደረጉ ግልጽ ያሆኑ ዋቢዎችን እናስወግዳለን።
እርከን 2 በመንግስት ወይም መከላከያ ተዋናዮች ላይ በትቅ ትግል የሚዋጉ ነገር ግን በማወቅ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ የማያደርጉ መንግስታዊ ያልሆኑ ተዋናዮች። ለወደፊት ግጭቶች የሚዘጋጁ ወይም የሚሰብኩ ነገር ግን እስካሁን በግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ጠብ አጫሪ ተቋማትንም ያካትታል። እነዚህ ተቋማት እንዲሁም የእኛን የጥላቻ ምግባር ወይም አደገኛ ድርጅት እና ግለሰቦች ፖሊሲዎችን በመድረኩ ላይ ወይም ከመድረኩ ውጪ በተደጋጋሚ ሊጥሱ የሚችሉ ተቋማትም ናቸው። እነዚህን ተቋማት፣ መሪዎቻቸውን፣ መስራቾቻቸውን ወይም ታዋቂ አባሎቻቸውን ማወደስ፣ ጉልህ ድጋፍን እና ውክልናን እናስወግዳለን።
ተጠቃሚዎች አደገኛ ተብለው የተፈረጁ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ግልጽነት አገባብ እነዚህን አካላት በማጣቀሻነት ያካተቱ ይዘቶችን ሊያጋሩ እንደሚችሉ እናውቃለን። ይህም አደገኛ ድርጅትን እና ግለሰቦችን ወይም እንቅስቃሴያቸውን ሪፖርት የሚያደርግ ይዘት፣ በንጹህ ልብ መወያየት ወይም ማውገዝን ያካትታል።
የዜና ዘገባዎች አደገኛ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የተሳተፉበት የአካባቢ እና ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች ግንዛቤን ለማሳደግ የሚጋራ መረጃን ያካትታል።
  • ለምሳሌ “ሰበር ዜና፡- በሶማሊያ ለተፈፀመው ጥቃት አልሸባብ ሃላፊነቱን ወስዷል”
  • ለምሳሌ "የአውደ ታሪክ እና የባለሙያዎች ትንታኔ፦ በቡፋሎ ሱፐርማርኬት የተኩስ ልውውጥ እንዴት ተከሰተ እና አጥፊው ​​በፍርድ ቤት ምን አለ"
ገለልተኛ ውይይት እንደ በተፈረጀው አደገኛ ድርጅት ወይም ግለሰብ እና በባህሪያቸው ዙሪያ አዎንታዊ ፍርድን የማይገልጹ ተጨባጭ መግለጫዎች፣ አስተያየቶች፣ ጥያቄዎች ያሉን እና ሌሎች መረጃዎች ያጠቃልላል።
  • ለምሳሌ "አልቃይዳ በአመራር እና በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከ ISIS ያነሰ ስጋትን ይወክላል"
  • ለምሳሌ "አንደር ብሬቪክ የአክራሪነት ሂደት ምን ያህል ውስብስብ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ነው"
ውግዘት ስለተመደበ አደገኛ ድርጅት ወይም ግለሰብ እና ባህሪያቸው አለመስማማትን፣ መጸየፍን፣ አለመቀበልን፣ ትችትን፣ ፌዝ እና ሌሎች አሉታዊ መግለጫዎችን ያጠቃልላል።
  • ለምሳሌ “የሳልቫዶር ራሞስ ወንጀል አስጸያፊ ሆኖ ይሰማኛል። የዳኛው ንግግር በጣም አስተጋባብኝ። በፍርድ ቤት ምሕረት ማግኘት የለበትም”
  • ለምሳሌ "የሂትለር ወንጀል መቼም ቢሆን አይረሳም። እነዚህ ከጨለማዎች የተወሰኑት ነበሩ”
የእኛ ፖሊሲዎች ለእነዚህ አይነት ውይይቶች ቦታ ለመስጠት የተነደፉ ሲሆኑ በተመሳሳይ ጊዜም ከመስመር ውጭ ጉዳቶች ሊያደርሱ የሚችሉትን አደጋዎች የሚገድቡ ናቸው። ስለዚህ ሰዎች እንደዚህ አይነት ይዘት ሲፈጥሩ ወይም ሲያጋሩ ሀሳባቸውን በግልፅ እንዲያሳዩ እንጠይቃለን። የተጠቃሚው ፍላጎት አሻሚ ከሆነ ወይም ግልጽ ካልሆነ፣ በነባሪነት ይዘትን እናስወግዳለን።
በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ህግ መሰረት፣ ፖሊሲዎቻችን አደገኛ ግለሰቦች ወይም አደገኛ ተብለው የተሰየሙ አካላት አባላት የሰብአዊ መብቶች ላይ ውይይት ለማድረግ ይፈቅዳል፣ ይዘቱ ሌላ አደገኛ ተብለው የተሰየሙ አካላትን ውዳሴ፣ ድጋፍን፣ ወይም ውክልናን ወይም እንደ ሁከት መቀስቀስ ያሉ ሌሎች የፖሊሲ ጥሰቶችን እስካላካተተ ድረስ።
እባክዎ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው የሰብዓዊ መብቶች ላይ ስላለን ቁርጠኝነት ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የእኛን የድርጅት የሰብዓዊ መብት ፖሊሲ ይመልከቱ።
የሚከተሉትን እናስወግዳለን፦
የተለያዩ አደገኛ ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን ማወደስ፣ መደገፍ እና መወከልን እናስወግዳለን። እነዚህ ንድፈ-ሀሳቦች ድርጅቶቹን፣ እንቅስቃሴዎቻቸውን እና አባላቶቻቸውን ይመለከታሉ። እነዚህ ንድፈ ሀሳቦች የሆነ ፖለቲካዊ ውጤት ለማምጣት የሚደረግ ሰላማዊ ድጋፍን አይከለክሉም።
ማወደስ፣ ከታች ባሉት በማንኛውም ይገለጻል፦
  • ድርጊቱ ተቀባይነት ያለው ወይም ምክንያታዊ የሚያደርጋቸው የሞራል፣ የፖለቲካ፣ የሎጂክ ወይም ሌላ ማረጋገጫ አላቸው በማለት የአንድን አካል የጥቃት ወይም የጥላቻ ድርጊቶች ህጋዊ ማድረግ ወይም መከላከል።
    • ለምሳሌ “ሂትለር ምንም ጥፋት አላጠፋም።”
  • የአንድ የተወሰነ አካል ጥቃትን ወይም ጥላቻን እንደ ስኬት መለየት ወይም ማክበር፤
    • ለምሳሌ “Hizbul Mujahideen ለነፃ እና ገለልተኛ ካሽሚር ጦርነቱን እያሸነፈ ነው”
  • የአባልነት ምኞት መግለጫ ወይም የተመደበ አካል ወይም የአመጽ ክስተት ፈጻሚ መሆን እንደሚፈልጉ የሚገልጽ መግለጫ።
    • ለምሳሌ " ISIS ን ተቀላቅዬ የኺላፋ አካል ብሆን ምኞቴ ነው"
ለእርከን 1 እና እርከን 2 ተቋማት እና ለተፈረጁ ክንውኖች የሚደረጉ ውደሳዎችን እናስወግዳለን።
ለእርከን1 እና ለተፈረጁ ክስተቶች፣ የተጠቃሚው አላማ በግልጽ ካልተቀመጠ ግልጽ ያልሆኑ ወይም አገባብ የሌላቸው ዋቢዎችን ልናስወግድም እንችላለን። ይህም እንደ ግልጽ ያልሆነ ቀልድ ወይም የተፈረጀውን ተቋም ብጥብጥ ወይም ጥላቻ የማያወድሱ የመግለጫ ጽሑፍ የሌላቸው ወይም አዎንታዊ ዋቢዎችን ያካትታል።
ድጋፍ፣ ከታች ባሉት በማንኛውም ይገለጻል፦
  • የቁሳቁስ ድጋፍ
    • የተፈረጀውን ተቋም የፋይናንስ ሁኔታ የሚያጠናክር ማንኛውም ድርጊት – ይህ ገንዘብን ለተፈረጀ ተቋም መስጠት፣ ወይም ከተቋሙ መውሰድ፤
      • ለምሳሌ፣ “ለኬኬኬ ይለግሱ!”
    • ማንኛውም ለተፈረጀ ተቋም ወይም ክንውን ቁሳዊ እርዳታ የሚያደርግ ድርጊት፤
      • ለምሳሌ፣ “የእንክብካቤ ጥቅሎችን ወደ ሲናሎአ ካርቴሎች ለመላክ ከፈለጉ፣ ይህንን አድራሻ ይጠቀሙ፦”
    • የተፈረጀ ተቋም ወይም ክንውንን በመወከል ምልመላ ማካሄድ፤
      • ለምሳሌ፣ “የካሊፌቱ ተዋጊ መሆን ከፈለጉ፣ ቀጥተኛ መልእክት ይላኩልኝ”
  • ሌላ ድጋፍ
    • ይፋዊ ተግባቦቶችን ጨምሮ፣ በተፈረጀ ተቋም ወይም ክንውን ፋንታ መረጃ ወይም መረጃዎችን ማመላለስ
      • ለምሳሌ፣ የተፈረጀ ተቋም ንግግርን የሚኮንን መግለጫ ሳያደርጉ በቀጥታ መጥቀስ፣ በገለልተኛነት መወያየት፣ ወይም የዜና ዘገባ አካል ማድረግ።
    • የተፈረጀ ተቋም ወይም ክንውንን በመወከል የድርጊት ጥሪ ማድረግ፤
      • ለምሳሌ “የአቶምዋፈን ክፍልን ያናግሩ - (XXX) XXX-XXXX”
ለእርከን 1 ሁሉንም ድጋፍ እና ለእርከን 2 የቁሳቁስ ድጋፍን እናስወግዳለን።
መወከል፣ ከታች ባሉት በማንኛውም ይገለጻል፦
  • የተፈረጀ ተቋም አባል መሆንዎ፣ ወይም የተፈረጁ ተቋም መሆንዎን መግለጽ፤
    • ለምሳሌ፣ “እኔ የኬኬኬ ታላቁ ድራጎን ነኝ።”
  • የተፈረጀ ተቋም የሆነ ወይም መሆኑን የሚያመላክት፣ ወይም በእሱ ፋንታ የሚሰራ፣ ወይም የተፈረጀ ክንውን መሆኑን የሚያሳይ ገጽ፣ ግለ-ማህደር፣ ክንውን፣ ቡድን፣ ወይም ሌላ የFacebook ተቋም መፍጠር።
    • ለምሳሌ፣ “የአሜሪካ ናዚ ፓርቲ” ተብሎ የተሰየመ ገጽ።
በእርከን 1 እና 2 የተፈረጁ ድርጅቶችን እና የተፈረጁ ክንውኖችን የሚወክሉ ውክልናዎችን እናስወግዳለን።
የአደገኛ ድርጅቶች አይነቶች እና እርከኖች
እርከን 1፦ ሽብርተኝነት፣ የተደራጀ ጥላቻ፣ መጠነ-ሰፊ የወንጀል እንቅስቃሴ፣ የጅምላ-የሚጎዳ ጥቃት ሙከራ፣ የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት፣ የጅምላ ግድያዎች፣ እና ጥሰት የሚፈጽሙ የጥቃት ክስተቶች
በሰሜን አሜሪካ መንግስት በልዩ ሁኔታ ናርኮቲክስ አዘዋዋሪ ኪንግፒንስ (SDNTKs) ተብለው የተሰየሙትን ጨምሮ፤ በጥላቻ፣ በሽብርተኝነት በሰሜን አሜሪካ መንግስት የውጪ አሸባሪ ድርጅቶች (FTOs) ወይም በልዩ ሁኔታ አለማቀፍ አሸባሪዎች (SDGTs) ተብለው የተሰየሙት ተቋማትን ጨምሮ፤ በተቀናጀ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በመድረኩ ላይ እንዲገኙ አንፈቅድም። ሌሎች ሰዎች እነዚህን ተቋማት እንዲወክሉም አንፈቅድም። የእነዚህ ድርጅቶች መሪዎች እና ታዋቂ አባላት መድረኩ ላይ እንዲኖሩ፣ እንዲሁም እነሱን የሚወክሉ አርማዎች፣ ወይም ግልጽ ያልሆኑ ዋቢዎችን ጨምሮ እነርሱን ወይም ድርጊቶቻቸውን የሚያደንቅ ይዘት መድረኩ ላይ እንዲኖር አንፈቅድም። በተጨማሪም፣ ለእነዚህ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚደረግ ድጋፍን እናስወግዳለን።
Meta እንደ የሽብር ጥቃቶች፣ የጥላቻ ክስተቶች፣ የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ወይም የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ሙከራን፣ የጅምላ ግድያዎችን፣ የጥላቻ ወንጀሎችን ወይም የጥሰት የሚፈጽሙ የጥቃት ክስተቶችን የሚያወድስ፣ የሚደግፍ ወይም የሚወክል ይዘትን አንፈቅድም። እንዲህ ያሉ ጥቃቶችን ያስተናበሩትን የሚያወድስ፣ የሚደግፍ ወይም የሚወክል (1) ይዘትንም አንፈቅድም። (2) ከእንደዚህ አይነት ጥቃቶች ጋር በተገናኘ በወንጀለኛ የመነጨ ይዘትን፤ ወይም (3) በሚታዩ ተጎጂዎች ላይ እንደዚህ ዓይነት ጥቃቶች የተፈጸሙበትን ጊዜ የሚያሳይ የሶስተኛ ወገን ምስሎችን አንፈቅድም።
በተጨማሪም፣ የተፈረጁ ጥላቻ አዘል ርዕዮተ ዓለሞችን ማወደስ፣ መደፈፍ ወይም መወከል እንዲሁም ግልጽ ያልሆነ ዋቢዎችን አንፈቅድም።
አሸባሪ ድርጅቶች እና ግለሰቦች፣ በሚከተለው መልኩ የሚገለጹ መንግስታዊ ያልሆኑ ተዋንያን ናቸው፦
  • ታልመው እና ታቅደው በሚሰሩ የብጥብጥ ድርጊቶች የሚሳተፉ፣ የምያበረታቱ፣ ወይም የማይናቅ ድጋፍ የሚሰጡ፣
  • ሲቪሎች ወይም በትጥቅ ግጭት ሁኔታ በግጭቶቹ እና/ወይም ከሲቪሎች ሞት፣ ከባድ ጉዳት ወይም የከፋ ጉዳት ጋር የተያያዘ የንብረት ውድመት ጋር በቀጥታ የማይሳተፍ ማንኛውም ሌላ ሰው ላይ ሞት፣ ጉዳት ወይም የከፋ ጉዳት የሚያስከትል ወይም ለማስከተል የሚሞክር
  • ሲቪል ሕብረተሰብ፣ መንግስት፣ ወይም አለማቀፍ ድርጅትን ለማስገደድ፣ ለማስፈራራት እና/ወይም ተጽእኖ ለማድረግ የሚያልም
  • የፖለቲካ፣ የሃይማኖት፣ ወይም የርዕዮተ ዓለም አላማ ለማሳካት የሚጥር።
የጥላቻ ተቋም፣ በተጠበቁ ባህሪያቸው ላይ በመመስረት በሌሎች ላይ ጥላቻን የሚያሰራጭ እና የሚያበረታታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተብሎ ይገለጻል። የተቋሙ እንቅስቃሴዎች ቢያንስ በሚከተሉት የተወሰኑ ባህሪያት ተለይተው ይታወቃሉ፦
  • በተጠበቁ ባህሪያቸው ላይ ተመስርተው ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃት፣ ማስፈራሪያ ንግግሮች ወይም አደገኛ የትንኮሳ ዓይነቶች፤
  • የጥላቻ ንግግርን በተደጋጋሚ መጠቀም፤
  • የጥላቻ ርዕዮተ ዓለም ወይም ሌሎች የተፈረጁ የጥላቻ ተቋማት ውክልና፣ እና/ወይም
  • ሌሎች የጥላቻ ተቋማትን ወይም የጥላቻ ርዕዮተ ዓለሞችን ማወደስ ወይም መደገፍ።
ወንጀለኛ ድርጅቶች፣ የሚከተሉትን የሚያደርጉ የሶስት ወይም ከሶስት በላይ ሰዎች ህብረት ተደርጎ ይገለጻል፦
  • በስም፣ ቀለም(ሞች)፣ የእጅ ምልክት(ቶች) ወይም የታወቀ መለያ ስር የተደራጁ፤ እና
  • የሰዎች ግድያ፣ የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር፣ ወይም ሰዎችን ጠልፎ መሰወር ላይ የተሳተፈ ወይም ለመሳተፍ የዛተ።
የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት እና የጅምላ ግድያዎች
  • በአንድ ክስተት ውስጥ እንደ ሞት ወይም ከባድ የአካል ጉዳት የሚገለጹ ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ጉዳቶችን ካስከተለ አንድን ክስተት የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ወይም የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ሙከራ እንደሆነ እንቆጥረዋለን። እንደዚህ አይነት ጥቃት የፈፀመ ማንኛውም ግለሰብ የጅምላ-ተጎጂ ጥቃት ወንጀለኛ እንደሆነ ወይም የወንጀል ሙከራ እንደፈፀመ ይቆጠራል።
  • በበርካታ አጋጣሚዎች ወይም ቦታዎች ላይ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ግድያዎችን የፈፀመ ማንኛውንም ሰው እንደ ጅምላ ገዳይ እንቆጥረዋለን።
የጥላቻ ርዕዮተ ዓለም
  • ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን የመፈረጅ አሰራራችን ባህሪ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ አንዳንድ በተፈጥሮአቸው ከሁከት ጋር ትስስር ያላቸው ርዕዮተ ዓለሞች እና እምነቶች መኖራቸውን እና በዙርያቸው የተሰባሰቡ ሰዎችን ለሁከት ወይም ሌሎች ሰዎችን በሕግ ከለላ በሚደረግላቸው መገለጫዎቻቸው ላይ ተመስርተው የማግለል እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ለማድረግ እንደሚሞክሩ ይገባናል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ፣ ርዕዮተ ዓለሙን በመፈረጅ ይህንን ርዕዮተ ዓለም የሚደግፍ ይዘትን ከመድረካችን ላይ እናስወግዳለን። እነዚህ ርዕዮተ ዓለሞች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
    • ናዚያዊነት
    • የነጭ የበላይነት
    • የነጭ ብሄርተኝነት
    • የነጭ ተገንጣይነት
  • ለእነዚህ ርዕዮተ ዓለሞች የሚደረግ ግልጽ ማወደስ፣ ድጋፍ፣ እና ውክልናን እናስወግዳለን፣ እንዲሁም ለእነዚህ የጥላቻ ርዕዮተ ዓለሞች እውቅና የሚሰጡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች እናስወግዳለን።
እርከን 2፦ ጠብ ጫሪ የመንግስት ያልሆኑ ተዋናዮች እና ጠብ አጫሪ ተቋማት
በMeta ሁከተኛ የመንግስት ያልሆኑ ተዋናዮች ወይም ጠብ አጫሪ ተቋማት ተብለው የተፈረጁ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በFacebook ላይ መገኘት፣ ወይም ሌሎች በእነርሱ ምትክ እንዲገኙ ማድረግ አይፈቀድላቸውም። እነዚህ ማህበረሰቦች ከመንግስት ወይም መከላከያ ተዋናዮች ጋር በጠብ ማጫር፣ በትጥቅ ትግል (ጠብ አጫሪ የመንግስት ያልሆኑ ተዋናዮች) ላይ በንቁነት ስለሚሳተፉ ወይም ለወደፊት ብጥብጥ ለመፍጠር እየተዘጋጁ ወይም እየሞገቱ ወይም ሁኔታዎችን እየፈጠሩ ስለሆነ ለእነዚህ ተቋማት የሚደረግ የቁሳቁስ ድጋፍ አይፈቀድም። እነዚህን ተቋማት ማወደስንም እናስወግዳለን።
ሁከተኛ መንግስታዊ ያልሆኑ ተዋንያን፤ የሚከተሉትን የሚያደርግ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆነ ተዋናይ እንደሆነ ይገለጻል፦
  • በትጥቅ ትግል ውስጥ እንደ ጠላት ሆኖ በቀጥታ በመሳተፍ እና በማወቅ እና ነጥሎ ሰላማዊ ሰዎችን በከፍተኛ-ክብደት ያለው ነውጥ ዒላማ የማያደርግ መንግስትን፣ መከላከያን ወይም ሌሎች የታጠቁ ቡድኖችን ዒላማ ያደረገ የታሰበበት እና የታቀደ ከፍተኛ-ክብደት ያለው ነውጥ ውስጥ የሚሳተፍ። እና/ወይም
  • ማህበረሰቦች ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን ወይም የተፈጥሮ ግብዓቶችን እንዳያገኙ የሚከለክል፤ እና/ወይም
  • ከሞት፣ ከባድ ጉዳት ወይም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ከማድረስ ጋር የማይገናኙ በመሰረተ ልማት ላይ ጉልህ ጉዳት ለማድረስ የታሰቡ የጥቃት ድግግሞሽ ላይ የሚሳተፍ።
ጠብ ጫሪ አካላት እንደሚከተለው ይገለጻሉ፦
ጠብ የሚጭር አካል (ባጠቃላይ) ማለት የሚከተለውን የሚያደርግ መንግስታዊ ያልሆነ ተዋናይ ማለት ነው፦
  • የራሱን ግብ ወይም የታለመ ተግባር ያደረገው፣ በዓመፅ አማካኝነት ከመንግሥት እውቅና ውጭ የሆነ የመንግሥት አስገዳጅ ተግባርን (እንደ ፖሊስ፣ ወታደራዊ፣ ወይም ኢሚግሬሽን ያሉ) በመንግሥት ምትክ ወይም በተጨማሪነት ለማከናወን፤ ወይም ደግሞ የመንግሥትን አስገዳጅ ተግባር በዓመፅ ለማስተጓጎል ነው፤
  • በMeta የመገናኛ አውታሮች ላይ ይህንን ለተቀመጠው ግብ ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ እርምጃ የወሰደ፤ እና
  • ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ግፍ ወይም ጥቃት ለመፈጸም በተደጋጋሚ ጊዜያት (በኢንተርኔት ወይም ከአውታረ መረብ ውጭ) በመዛት ወይም በማነሳሳት ድርጊት ላይ የተሳተፈ፤
በጥላቻ የታገደ ተቋም ማለት የሚከተለውን የሚያደርግ መንግስታዊ ያለሆነ ተዋናይ ማለት ነው፦
  • በተደጋጋሚ የጥላቻ ባህሪ ወይም ንግግር ላይ የሚሳተፉ ተቋማት ተብለው የሚገለጹ ሆነው፣ ሁከት ላይ በተግባር ያልተሳተፉ ወይም በግልጽ ሁከትን ያላበረታቱ በመሆናቸው ምክንያት፣ ወይም ከዚህ ቀደም ከተፈረጁ ድርጅቶች ወይም ታዋቂ ሰዎች በቂ ግንኙነት የሌላቸው በመሆናቸው ምክንያት እርከን 1 አካል ላይ ያልደረሱ አካላት።
ለሚከተሉት የማህበረሰብ ደንቦች፣ ተግባራዊ ለማድረግ ተጨማሪ መረጃ እና/ወይም አውድ እንፈልጋለን፦
  • በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ይዘቱ የምጸት መሆኑ ሲታወቅ የማህበረሰብ ደንቦችን ሊጥስ የሚችል ይዘትን እንፈቅዳለን። ይዘቱ የሚፈቀደው የሚጥሱት የይዘቱ ክፍሎች ለማሳቅ የታሰቡ ከሆነ ወይም የሆነ ነገርን ወይም ሌላ ሰውን ለመሳለቅ ወይም ለመተቸት የታሰቡ ከሆነ ብቻ ነው።
የተጠቃሚ ተሞክሮዎች
Facebook ላይ ላሉ ሰዎች ደንብ ማስከበር ምን እንደሚመስል አንዳንድ ምሳሌዎችን ይመልከቱ፣ ለምሳሌ፦ Facebook ላይ መሆን የለበትም ብለው የሚያምኑትን የሆነ ነገር ሪፖርት ማድረግ፣ የማህበረሰብ ደንቦችን ጥሰዋል ተብሎ ሲነገርዎ እና የሆነ ይዘት ላይ የማስጠንቀቂያ ማያ ገጽ ማየት ምን እንደሚመስል።
ማስታወሻ፦ እኛ ሁልጊዜም በመሻሻል ላይ ነን፣ ስለዚህ እዚህ የሚያዩት ነገር አሁን ከምንጠቀምበት ነገር አንጻር ትንሽ ጊዜው ያለፈበት ሊሆን ይችላል።
የተጠቃሚ ተሞክሮ
ሪፖርት ማድረግ
የተጠቃሚ ተሞክሮ
የድህረ-ሪፖርት መረጃ ልውውጥ
የተጠቃሚ ተሞክሮ
የማስወገድ ተሞክሮ
የተጠቃሚ ተሞክሮ
የማስጠንቀቂያ ማያ ገጾች
ውሂብ
የቅርብ ጊዜውን የማህበረሰብ ደንቦች ማስፈጸሚያ ሪፖርት ይመልከቱ
ማስፈጸም
በዓለም ዙሪያ በFacebook ላይ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ ሰው ተመሳሳይ ፖሊሲዎች አሉን።
የግምገማ ቡድኖች
በመላ ዓለም የሚገኙ ከ15,000 በላይ ገምጋሚዎችን ያቀፈ ቡድናችን Facebook ላይ የሚገኙ ሰዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ስራዎችን ይሰራል።
የባለድርሻ ተሳትፎ
ውጫዊ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ፖሊሲ አውጪዎች የFacebook የማህበረሰብ ደንቦችን ለማሳወቅ ይረዳሉ።
አደገኛ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን በተመለከተ እገዛ ያግኙ
የማህበረሰብ ደንቦቻችንን የሚጻረር ነገር በFacebook ላይ ካዩ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይወቁ።
የእገዛ ማዕከላችንን ይጎብኙ