የልጆች ወሲባዊ ብዝበዛ
የህፃናት ወሲባዊ ብዝበዛን (እውነተኛ ታዳጊዎችን፣ ህጻናት ወይም ጨቅላ ሕፃናትን ወይም የሰው አምሳያ ያላቸው እውነተኛ ያልሆኑ ሥዕሎች፣ ለምሳሌ በጥበብ ስራ፣ በ AI የመነጨ ይዘት፣ ልብ ወለዳዊ ገፀ-ባህሪያት፣ አሻንጉሊቶች፣ ወዘተ ያሉትን ጨምሮ) የሚያስፈራ፣ የሚገልጽ፣ የሚያመሰግን፣ የሚደግፍ፣ መመሪያ የሚሰጥ፣ የፍላጎት መግለጫዎችን የሚያደርግ፣ ተሳትፎን የሚያምን ወይም የልጆች ወሲባዊ ብዝበዛን የሚያጋራ ይዘት፣ እንቅስቃሴ፣ ወይም መስተጋብሮች። ይህ የሚከተሉትን ያካትታል ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰንም፦
የግብረ-ስጋ ግንኙነት
ግልጽ የግብረ-ስጋ ግንኙነት ወይም የአፍ ግብረ-ስጋ፣ ማለትም ቢያንስ የአንድ ሰው ብልቶች ወይም ፊንጢጣ በሚታይበት ሁኔታ ወደ አፍ ወይም ወደ ብልት ማስገባት ወይም ከሌላ ሰው ብልት ወይም ፊንጢጣ ጋር ንክኪ ማድረግ።
የግብረ ሥጋ ግንኙነት አመላካች ወይም የአፍ ወሲብ፣ ንክኪው የማይቀር ወይም በቀጥታ የማይታይበትን ጨምሮ።
ብልትን ወይም ፊንጢጣ ማነቃቃት፣ እንቅስቃሴው ሊደረግ ሲል ወይም በቀጥታ የማይታይበትን ጨምሮ።
ከላይ ከተዘረዘሩት መካከል እንስሳትን የሚመለከት ማንኛውም።
ወሲባዊ አካላት ያላቸው ህፃናት፣ የሚከተሉትን ጨምሮ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ ሳይገደብ፦
እስራት
የመቀስቀስ ምልክቶች
የብልት አካላት ወይም ፊንጢጣ ላይ ማተኮር
ወሲባዊ ስሜት ውስጥ የገባ አዋቂ መኖር
የወሲብ መጫወቻዎች መኖር ወይም ማንኛውንም ነገር ለወሲብ ማነቃቂያ፣ እርካታ፣ ወይም ወሲባዊ በደል መጠቀም
ወሲባዊነት የሚያንጸባርቅ አለባበስ
ልብስ ማውለቅ
የተመቻቸ ቦታ (ለምሳሌ፣ አልጋ ላይ) ወይም በሙያዊ ብቃት የተነሳ ምስል (ጥራት/ትኩረት/መአዝኖች)
በክፍት አፍ መሳሳም
የሰውን የጡት ጫፍ ማነቃቃት ወይም የሴት ጡትን መጭመቅ (ከጡት ማጥባት አውድ በስተቀር)
የወሲባዊ እንቅስቃሴ ተረፈ ውጤት መኖር
በልዩ ወሲባዊ ፍላጎት አውድ ዉስጥ ህፃናትን የሚያካትት ይዘት
በጤና አውድ ውስጥ ገለልተኛ በሆነ ሁኔታ ካልተወያዩ በስተቀር በፔዶፊሊያ ውስጥ ተሳትፎን የሚደግፍ፣ የሚያሳድግ፣ የሚሟገት ወይም የሚያበረታታ ይዘት።
በልጆች ወሲባዊ ብዝበዛ ሰለባ ናቸው የተባሉትን በስም ወይም በምስል የሚለይ ወይም የሚያሾፍ ይዘት
ወሲባዊ ማባበያ
ወሲባዊ ይዘትን የሚጠይቅ ይዘት ወይም ህፃናትን የሚያሳይ ወይም የሚያሳትፍ ተግባር፣ እንደ የሚከተለው ይገለጻል፦
የህፃን ወሲባዊ ጥቃት ቁሳቁስ (CSAM)
የእውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ የህፃናት እርቃን ምስሎች
የእውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ የህፃናት ወሲባዊ ምስሎች
ከህፃናት ጋር ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት
ከልጆች ጋር ተገቢ ያልሆኑ ግንኙነቶችን የሚያካትት ወይም የሚያመቻች ይዘት፣ ለምሳሌ፡-
ከልጆች ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነትን መጠየቅ፣ ማደራጀት ወይም ማቀድ
ወሲባዊ በተደረጉ ውይይቶች ወይም ግብዣዎች ልጆች በወሲባዊ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማነሳሳት፣ በታቀደ ልቀት ወይም በግል መልዕክቶች ውስጥ ከልጆች ወይም ለልጆች ወሲባዊ ቁሳቁስ ማሳየት፣ ማግኘት ወይም መጠየቅ
ከህጻናት ጋር በግላዊ መልእክቶች አማካኝነት ቀጥተኛ ያልሆኑ ወሲባዊ የሃሳብ ልውውጦች ማድረግ
በግላዊ መልእክት አማካኝነት ወሲባዊ ቁሳቁስ ከህጻናት መውሰድ ወይም መጠየቅ
በዝባዥ ወሲብ ነክ ምስሎች እና ወሲብ ነክ እንቅስቃሴን የማጋለጥ ማስፈራሪያ ብዝበዛ
ትክክለኛ ህጻናትን ለመበዝበዝ የሚሞክር ይዘት በ፦
እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ የሰዎችን ቅርብ የፍቅር ምስል ወይም መረጃ አጋልጣለሁ ብሎ ሰዎችን በማስፈራራት አስገድዶ ገንዘብ ለመውሰድ፣ ውልታ ለማግኘት፣ ወይም የቅርብ ፍቅር ምስል ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት
የግል ወሲባዊ ውይይቶችን ወይም እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ወሲብ ነክ ምስሎችን ማጋራት፣ ለማጋራት ማስፈራራት ወይም ፍላጎት መግለፅ።
ህፃናትን ወሲባዊነት ማላበስ
እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ህፃናትን ወሲባዊነት የሚያላበስ ይዘት (ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ የገሀዱ-ዓለም ጥበብን፣ ዲጂታላዊ ይዘት እና ንግግራዊ አገላለጾችን ጨምሮ)።
እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ልጆችን ወሲባዊነትን ለማላበስ የሚሰሩ ቡድኖች፣ ገጾች፣ እና ግለ ማህደሮች።
የልጆች እርቃን ምስል
እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ልጆችን እርቃንነት የሚያሳይ ይዘት፣ እርቃንነት እንደሚከተለው የሚገለጽ ሆኖ፦
የእውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ህፃናትን ብልቶች አጉልቶ የሚያሳይ
የሚከተሉትን የሚያሳዩ እርቃናቸዉን የሆኑ እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ታዳጊዎች፦
የብልት አካላት የምያሳይ ብርሃን በምያሳልፍ ወይም በምያሳይ አልባሳት ቢመሸፈን ወይም ቢደበዝዝ እንኳን
የሚታይ ፊንጢጣ እና/ወይም ምሉበሙሉ እርቃኑ የወጣ ጎልቶ የሚታይ ቂጥ
የሚከተሉትን የሚያሳዩ እርቃናቸዉን የሆኑ እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ህጻናት፦
የሚታይ የብልት አካል (በጭገር ወይም ብርሃን በሚያሳልፍ አልባሳት ብቻ የደበዝዘ ብልትን ጨምሮ)
የሚታይ ፊንጢጣ እና/ወይም ምሉበሙሉ እርቃኑ የወጣ ጎልቶ የሚታይ ቂጥ
ያልተሸፈኑ የሴቶች የጡት ጫፎች
ከአንገት እስከ ጉልበት ምንም ልብስ የለም - ምንም እንኳን የጾታ ብልት ወይም የሴቶች የጡት ጫፎች ባይታዩም
እውነተኛው ያልሆነው ምስል ለጤና ዓላማ ካልሆነ ወይም የሕፃን እርቃንነት በእውነተኛ ቃል ጥበብ ውስጥ ወሲባዊ ያልሆነ ምስል ካልሆነ በስተቀር
ወሲባዊ ያልሆነ የህጻን ብዝበዛ
ምስሉ ከገሃዱ ዓለም ጥበብ፣ ካርቱኖች፣ ፊልሞች ወይም የቪዲዮ ጨዋታዎች ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆነ ወሲባዊ ያልሆነ የልጅ ጥቃትን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ወይም ፎቶዎች የተጋራበት ሃሳብን ምንም ይሁን ምን
ወሲባዊ ያልሆነ የልጆች ጥቃት ላይ የሚደረግን ተሳትፎ የሚያደንቅ፣ የሚያግዝ፣ የሚያስተዋውቅ፣ የሚሟገት፣ ለዚህ ተሳትፎ የሚሆን መመሪያ የሚሰጥ ወይም የሚያበረታታ ይዘት።