Meta ውስጥ፣ ሰዎች ድምጻቸው እንዲሰማ ለማገዝ እና ደኅንነታቸው የተጠበቀ አድርጎ ለማቆየት ቁርጠኞች ነን።

ከ2016 ጀምሮ፣ በመላው የMeta ቴክኖሎጂዎች ላይ ይዘትን ለማስተዳደር «አስወግድ፣ ቀንስ፣ አሳውቅ» የተሰኘ ስትራቴጂ ተጠቅመናል።
ይህ ማለት ከእኛ ፖሊሲዎች በተቃራኒ የሚሄዱ ጎጂ ይዘቶችን እናስወግዳለን፣ የእኛን ፖሊሲዎች የማይጥሱ ነገር ግን ችግር ያለባቸውን ይዘቶች ሥርጭት እንቀንሳለን፣ እንዲሁም ሰዎች የትኛውን ጠቅ ማድረግ እና የትኛውን ማጋራት እንዳለባቸው መወሰን እንዲችሉ ተጨማሪ ዐውድ ለመስጠት መረጃ እንሰጣቸዋለን።
ይህንን ስትራቴጂ ለመደገፍ በቴክኖሎጂዎቻችን ላይ ምን እንደሚፈቀድ እና እንደማይፈቀድ የሚያብራሩ ፖሊሲዎች አሉን። ቡድኖቻችን ፖሊሲዎቻችንን ለማዘጋጀት እና ለማስፈጸም በጋራ ይሠራሉ። እንዴት እንደሚሠራ እነሆ።

1

ፖሊሲዎቻችንን ለመፍጠር እና ለማዘመን በቴክኖሎጂ፣ በሕዝብ ደኅንነት እና በሰብአዊ መብቶች ላይ ከዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር እንተባበራለን።

2

ሰዎች ይዘትን ሪፖርት እንዲያደርጉ እና መለያዎችን እንዲያግዱ፣ እንዲደብቁ ወይም መከተል እንዲያቆሙ የደኅንነት ባህሪያትን እንገነባለን።

3

ፖሊሲዎቻችንን የምናስፈጽመው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወይም በሰው ኃይል በማስገምገም ነው።
የሰዎችን ደኅንነት እንጠብቃለን፣ እንዲሁም ፖሊሲዎቻችንን፣ የማስፈጸም እና የግልጽነት ሪፖርቶችን በማጋራት ሰዎች በተጠያቂነት እንዲይዙን እንፈቅዳለን።
policy-image
ፖሊሲዎቻችን
ፖሊሲዎቻችን በFacebook ቴክኖሎጂ ላይ ምን እንደሚፈቀድ እና እንደማይፈቀድ ይገልጻሉ። አንድ ይዘት ከእኛ ፖሊሲዎች በተቃራኒ የሚሄድ ከሆነ፣ እርምጃ እንወስድበታለን።
enforcement-image
የማስገደድ እርምጃዎቻችን
በFacebook እና በInstagram ላይ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የይዘት ቅንጣቶችን ለማግኘት፣ ለመገምገም እና እርምጃ ለመውሰድ ቴክኖሎጂን እና የግምገማ ቡድኖችን እንጠቀማለን።
transparency-reports-image
የግልጽነት ሪፖርቶቻችን
ፖሊሲዎቻችንን በማስፈጸም ረገድ ምን እያደረግን እንደሆነ ለሰዎች ለማሳየት መደበኛ የግልጽነት ሪፖርቶችን እናትማለን።
ranking-image
ደረጃ አሰጣጥን ለማብራራት ያለን አቀራረብ
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሥርዓቶች በMeta ምርቶች ላይ ለብዙ ተሞክሮዎች የይዘት ደረጃ አሰጣጥን ያሳውቃሉ፣ ለምሳሌ Facebook ምግብን መመልከት፣ Instagram ላይ ሪሎችን መመልከት ወይም Facebook Marketplaceን ማሰስ።
የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎች